ሞግዚት(አሳዳጊ) ያልሆኑ ወላጆች ሁሉንም የታዘዘውን የልጅ ድጋፍ ክፍያዎችን የመክፈል ሀላፊነት አለባቸው።  ሞግዚት (አሳዳጊ) ያልሆኑት ወላጅ ይህን ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያግዙ ፕሮግራሞች እና ሌሎች መረጃዎች አሉ።
ሞግዚት(አሳዳጊ) ያልሆነ ወላጆች እና አሰሪዎች የልጅ ድጋፍ ክፍያዎችን የሚያደርጉበት የተለያዩ ዘዴዎች አሉ።

Clearinghouse (ክሊሪንግሀውስ)
የCSSD Clearinghouse(ክሊሪንግሀውስ) ክፍያዎችን ይስፈጽማል፣ ይህም ክፍያዎችን መቀበል፣ ክፍያዎችን መክፈል፣ እና ክፍያዎችን ማከፋፈልን ያካትታል።  በተጨማሪ ክሊሪንግሀውሱ (እንደ አግባብነቱ) የአሰሪ መረጃን ወቅታዊ ያደርጋል። በCSSD በኩል ስለተከፈሉ የክፍያ መረጃዎች በCSSD አውቶሜትድ ሲስተሞች በአንዱ አማካኝነት ሊገኝ ይችላል።

የልጅ ድጋፍን በፖስታ መክፈል
የገንዘብ መክፈያ ትእዛዞች ወይም ቼኮችን መከፈል አለበት ለ፣ “District of Columbia (DC) Child Support Clearinghouse.”  መረጃው በግልጽ መጻፍ አለበት፣ እና የከፋዩን ስም፣ የመዝገብ ቁጥር፣ እና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሩን መያዝ አለበት።
የገንዘብ ማዘዣዎች እና ቼኮች ወደ ተገቢው የፖስታ ሳጥን በፖስታ እንደሚከተለው መላክ አለበት፣

ሞግዚት(አሳዳጊ) ያልሆኑ ወገኖች፣
DC CHILD SUPPORT CLEARINGHOUSE(የዲሲ የልጅ ድጋፍ ክሊሪንግሀውስ)
PO Box 37715
Washington, DC 20013-7715

አሰሪዎች
DC CHILD SUPPORT CLEARINGHOUSE(የዲሲ የልጅ ድጋፍ ክሊሪንግሀውስ)
PO Box 37868
Washington, DC 20013-7868

ሌሎች የስቴት ኤጀንሲዎች
DC CHILD SUPPORT CLEARINGHOUSE(የዲሲ የልጅ ድጋፍ ክሊሪንግሀውስ)
PO Box 37789
Washington, DC 20013-7789

የልጅ ድጋፍን በኤሌክትሮኒክ መንገድ መክፈል
የልጅ ድጋፍ ክፍያዎችን በኢንተርኔት መክፈል ይቻላል በ  dc.SmartChildSupport.com
ያስተውሉ፣ የመጀመሪያው ክፍያ ወዲያውኑ አይሆንም። አካውንትዎን ለመክፈት ከሰባት እስከ አስር የሥራ ቀናት ይወስዳል። አካውንትዎ ከተዘጋጀ በኋላ፣ በማናቸውም ጊዜ ክፍያ መክፈል ይችላሉ።

ተያያዥ ይዘቶች፣
አሰሪዎች
የገንዘብ ብሮሸርዎን ማስኬድ

Related Content: