የተገልጋይ ማስጠንቀቂያ፣ ኮሮናቫይረስ (COVID-19)፣ መብቶችዎን ይወቁ

Consumer Alert Banner

 

የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (Office of the Attorney General, OAG) የኮሮናቫይረስ (COVID-19) የህዝብ ጤና ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ ነው እና ዛሬ በከንቲባው የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እይተገበረ ነው። በተጨማሪ OAG በበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከሎች (Centers for Disease Control and Prevention, CDC) እና በግዛቱ የጤና ዲፓርትመንት የተሰጡ መመርያዎችን እየመረመረ ነው። የግዛቱ ኗሪዎች መብታቸው ማወቃቸውን ለማረጋገጥ፣ እዚህ ለደምበኞች የተወሰኑ ስለ ሀሰተኛ መረጃ፣ ማጭበርበሮች፣ እና የዋጋ መለኪያዎች ጠቃሚ ምክሮች አሉ፣ እንዲሁም ለሰራተኞች ከደሞዝ ጋር የህመም የእረፍት ፍቃድ ጠቃሚ ምክሮች፣ እና ስለኮሮናቫይረስ (COVID-19) ነጻ የሆኑ የጤና ግብአቶች።

እራስዎን ከመጭበርበር ይጠብቁ

Scam icon

አጭበርባሪዎች በሽታውን ለመከላከል የማይችሉ ምርቶችን በመሸጥ እና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች ቻናሎችን በመጠቀም በማሰራጨት ተገልጋዮችን ለማጭበርበር ሊሞክሩ ይችላሉ። ሌሎች አጭበርባሪዎች የኮሮናቫይረስ ሰለባዎችን ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ የሚያሰባስቡ በመምሰል፣ የተገልጋዮችን ገንዘብ እና የግል መረጃ ሊሰርቁ ይችላሉ።

የሚከተሉት እራስዎን ከእንደዚህ አይነት ማጭበርበሮች የሚጠብቁበት የተወሰኑ ጠቃሚ ምክሮች ናቸው፣

  • ከ CDC እንደተላኩ የሚገልጹ ኢሜይሎችን ወይም ስለቫይረሱ መረጃ እንዳላቸው የሚገልጹ ኤክስፐሮቶች ነን የሚሉትን ተጠንቀቋቸው። ስለኮሮናቫይረስ እና የመከላከያ ጠቃሚ ምክሮችን አስመልክቶ አዳዲስ መረጃን በተመለከተ፣ በበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከሎች (CDC) እና የ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ይጎብኙ።
  • ስለመከላከል እና ህክምና በተመለከተ ያሉትን ጥያቄዎች የህክምና ባለሞያ ያማክሩ። ክትባት እንሰጣለን የሚሉ ጥያቄዎችን ምላሽ አይስጧቸው እና ለበሽታው መድሀኒት ወይም ህክምና አለን የሚሉ ማስታወቂያዎችን ይጠንቀቁ። በኮሮናቫይረስ ከመያዝ ለመከላከል ተመራጩ መንገድ ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆንን መከላከል ቢሆንም እንኳን፣ CDC እና  DC የጤና ዲፓርትመንት  በትንፋሽ የሚተላለፉ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች አሏቸው።
  • ለምግባረሰናይ ድርጅት ከመለገስዎ በፊት የራስዎን ማጣራት ያድርጉ። አንድ ድርጅት “CDC”  ወይም “መንግስት” የሚለውን ቃላቶች ስሙ ላይ በመጠቀሙ ምክንያት ወይም እቃዎቹ ላይ የሚታወቅ የሚመስል ማህተሞች ወይም አርማዎች ስላሉት ብቻ ትክክለኛ ላይሆን እንደሚችል ያስታውሱ። አንድ ምግባረሰናይ ድርጅት ህጋዊ መሆኑን የሚያረጋግጡበት ገለልተኛ የሆኑ የተለያዩ የኦንላይን ምንጮች አሉ። የOAG ነጻ የመማርያ ግብአቶችን ተጠቅመው ለእርዳታ በሚል የማጭበርበር ተግባር ሰለባ እንዳይሆኑ የሚከላከሉበትን ተጨማሪ ምክሮች ይማሩ
  • የማጭበርበር ተግባሮችን ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ ሪፖርት ያድርጉ (OAG)፣ እርስዎ የማጭበርበር ሰለባ እንደሆኑ ካመኑ፣ ለOAG በ 202-442-9828 በመደወል፣ በ consumer.protection@dc.gov ኢሜይል በማድረግ፣ ወይም  የኦንላይን ቅጽ ያስገቡ።

OAG የግዛቱ ኗሪዎች የተገልጋይ መብቶቻቸውን እንዲያውቁ ማስተማር ላይ ይሰራል፣ የግለሰብ የተገልጋይ አቤቱታዎች ላይ ምላሽ ይሰጣል፣ እና አስፈላጊ ሲሆን የህግ ማስከበር እርምጃዎችን ይወስዳል።

የዋጋ ማሻቀብን ሪፖርት ማድረግ

Dollar sign icon

የዛሬውን የከንቲባውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅን ተከትሎ የኮሎምቢያ ግዛት  የተፈጥሮ አደጋ የተገልጋይ የጥበቃ ህግ  አሁን ስራ ላይ ነው። የግዛቱ ህግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ካምፓኒ ተመሳሳይ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከከንቲባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከ90 ቀናት በፊት ከነበረው ዋጋ ጨምረው እንዳይሸጡ ይከለክላል (ለምሳሌ፣ ሳኒታይዘር (ማጽጃ)፣ ሶፍት፣ የጽዳት እና የጸረተህዋስ ምርቶች፣ እና ሌሎችን ዋጋ እንዳይጨምሩ)። ይህን ህግ የሚጥሱ ግለሰቦች እና ካምፓኒዎች ለእያንዳንዱ ጥሰት በ$5,000 የገንዘብ መቀጮ እና በንግድ ፍቃድ ስረዛ ይቀጣሉ። 

አቤቱታዎን ያስገቡ፣ OAG ዋጋ ስለማሻቀብ የሚቀርቡ የተገልጋይ አቤቱታዎችን የሚመረምሩ አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ቡድን አቋቁሟል። እርስዎ ከሚገባው ዋጋ በላይ እንዲከፍሉ መደረግዎን ካመኑ፣ የዋጋ ማሻቀብን ለ OAG ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ በ ፣

ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም የእረፍት ፍቃድ ብቶችዎን ይወቁ

Calendar icon

የግዛቱ Sick and Safe Leave Act (SSLA) (የህመም እና የደህንነት ፍቃድ ህግ) አብዛኛው አሰሪዎች ለሰራተኞች ደሞዝ የሚክፈልበት የህመመ እረፍት ፍቃድ እንዲሰጡ ይጠይቃል፣ ይህም ሰራተኞች በህመም ምክንያት ደሞዝ የሚከፈልበት ፍቃድ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል። የሚከተሉት ስለ SSLA አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ናቸው፣

  • ሰራተኞች ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ እንዴት ያገኛሉ? ሰራተኞች ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ የሚያገኙት በሰሩት ሰዓት ብዛት ነው። ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም የእረፍት ፍቃድ መጠን የሚወሰነው በአሰሪው መጠን ነው እና ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ ተጠቃሎ ቀርቧል፣
Paid Sick Leave Table Amharic
  • ሰራተኞች ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ መቼ መጠቀም ይችላሉ? ሰራተኞች ለአሰሪዎቻቸው ለ90 ቀናት ያክል ከሰሩ በኋላ ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ መጠቀም ይችላሉ።
  • ሰራተኞች ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድን ለምን ሊጠቀሙበት ይችላሉ? ሰራተኞች ለአካል ወይም የአእምሮ በሽታ ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ መውሰድ ይችላሉ። በተጨማሪ SSLA ሰራተኞች ለሌሎች አለማዎች  የአካል ወይም የአእምሮ ህመም ያጋጠማቸውን የቤተሰብ አባሎችን ለመንከባከብ እና የህክምና ምርመራ ወይም እንክብካቤ (የመከላከል ህክምናን ጨምሮ) ለማግኘት ደሞዝ የሚከፍልበት የህመም እረፍት ፍቃድን እንዲወስዱ ይፈቅዳል።
  • እኔ በSSLA ውስጥ ያሉኝ ሌሎች መብቶች ምንድን ናቸው?  ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ መብት ነው እና አሰሪዎች ሰራተኞች የሚገባቸውን ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም የእረፍት ፍቃድ ስለወሰዱ ማባረር፣ መቀነስ፣ ወይም የስነምግባር እርምጃ ሊወስዱባቸው አይችሉም።  
  • የ SSLA ጥሰቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ እችላለሁ? እርስዎ ደሞዝ የሚከፈልበት የህመም እረፍት ፍቃድ መብቶችዎ እየተጣሱ መሆኑን ካመኑ፣ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮን በ202-442-9828 በመደወል ያግኙ። ሰራተኞች በግዛቱ ህግ ያላቸውን መብቶች እና መብቶቻቸው ከተጣሱ እርዳታ እንዴት ማግኘት እንዳለባቸው በ https://oag.dc.gov/workers-rights መማር ይችላሉ።

 

OAG የመብት ጥሰት የሚፈጽሙ አሰሪዎችን በስርቆት ወንጀል ይጠይቃል፣ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰራተኞች ደሞዝ ያስመልሳል፣ እና ለሰራተኞች ስለመብቶቻቸው ያስተምራቸዋል።

የሲቪል መብቶች ጥበቃዎችዎን ይረዱ

Civil Rights Icon

የግዛቱ የንግድ ድርጅቶች አሁን ያለው የህዝብ ጤና ቀውስ ቢኖርም እንኳን ተገልጋዮችን እና ሰራተኞችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ አለባቸው።

  • የግዛቱ ህግ አሰሪዎች የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰራተኞች ምክንያታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን እንዲያቀርብ ይጠይቃል። ለምሳሌ፣ በሽታ የመቋቋም አቅማቸውን የሚያዳክም የህክምና ሁኔታ ስላላቸው ቤት ሆነው ለመስራት የሚጠይቁ ሰራተኞችን ፍላጎት በተቻለ አቅም ማሟላት አለበት።
  • የግዛቱ ህጎች የንግድ ድርጅቶች በተገልጋዮች እና ሰራተኞች ላይ መገለል እንዳይኖር ይከለክላል። ለምሳሌ፣ የግዛቱ የንግድ ድርጅቶች የተለየ የዘር ቡድኖች ያላቸውን ወይም ከተለየ የውጭ ሀገሮች የመጡ ሰዎች ላይ ዘራቸውን እና ብሄራዊ ምንጫቸውን አስመልክቶ ባላቸው የተለየ አመለካከት ምክንያት ማግለል አይችሉም።
  • መገለልን ሪፖርት ያድርጉ፣ ማንኛውም አይነት መገለል ካጋጠምዎ፣ ለOAG በ 202-727-3400 በመደወል፣ በOAGCivilRights@dc.gov ኢሜይል በማድረግ፣ ወይም የኛን የኦንላይን ቅጽ በመሙላት ሪፖርት ያድርጉ። በተጨማሪ አቤቱታዎን በ DC (ዲሲ) የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በ  ኦንላይን የሲቪል መብቶች የአቤቱታ ቅጽ  አማካኝነት ማቅረብ ይችላሉ ።

ለ D.C. (ዲሲ) ኗሪዎች አዲስ የድንገተኛ ጊዜ ጥበቃዎች

Emergency legislation

በ D.C. (ዲሲ) ምክር ቤት በወጣው አዲስ ህግ መሰረት፣ ተከራዮች በህዝብ የጤና አደጋዎች ጊዜ አዲስ ጥበቃዎች አሏቸው።

ለተከራዮች ጥበቃዎች

  • ባለቤቶች የመኖርያ ወይም የንግድ ተከራዮችን ማስለቀቅ አይችሉም ። አስቀድሞ ለማስለቀቅ የቀረቡ ጥያቄዎች ባሉበት ይቆያሉ እና ምንም አዲስ የማስለቀቅ ጥያቄዎች ሊቀርቡ አይችሉም።
  • ባለቤቶች ከንቲባው የህዝብ ጤና አደጋዎች ባወጁበት ጊዜ ላለ ማንኛውም ወር የመዘግየት ክፍያዎች ማስከፈል አይችሉም

ለተገልጋዮች ጥበቃዎች

  • የአገልግሎት ካምፓኒዎች የእርስዎን የጋዝ፣ የውሃ ወይም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማቋረጥ አይችሉም
  • ካምፓኒዎች እና ግለሰቦች አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን እንደ ሳኒታይዘር( የእጅ ማጽጃ)፣ በህገወጥ መልኩ ማከማቸት አይችሉም ። ይህን የማከማቸት አንቀጽ መጣስ ለእያንዳንዱ ጥሰት $ 5,000 መቀጮ ያስከትላል።

የእነዚህን ጥበቃዎች ጥሰቶች ለOAG ሪፖርት ያድርጉ በ
(202) 442-9828 በመደወል፣ ኢሜይል በማድረግ በ  
Consumer.Protection@dc.gov ወይም  በመስመር ላይ ቅሬታ

የጀርሞችን ስርጭት ይከላከሉ

Medical icon

በኮሮናቫይረስ ከመያዝ ለመከላከል ተመራጩ መንገድ ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆንን መከላከል ቢሆንም እንኳን፣ CDC እና  DC የጤና ዲፓርትመንት  የጀርሞችን ስርጭት መከላከል የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች አሏቸው።

  • እጆችን ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች ያክል በሳሙና እና በውሃ በቀን ውስጥ በርካታ ጊዜ ይታጠቡ። ሳሙና እና ውሃ የማይገኝ ከሆነ የአልኮል መሰረት ያለው የእጅ ማጽጃ መጠቀም ይቻላል
  • ባልታጠቡ እጆች አይኖችን፣ አፍንጫ እና አፍን ከመንካት መቆጠብ
  • ከታመሙ ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳይኖርዎ ያድርጉ
  • ሲታመሙ ቤትዎ ይቆዩ
  • ሳልዎን ወይም ማስነጠስዎን በሶፍት ይሸፍኑ፣ እና ከዚያ ሶፍቱን ቆሻሻ መጣያ ላይ ይጣሉ
  • አዘውትረው የሚነኩ እቃዎችን እና ስፍራዎችን ያጽዱ እና ጸረተህዋስያን ያድርጉበት
Stop Spread of Germs in Multiple Languages